የስራ ታሪክ

ክንውኖች

ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ የህብረት ስራ ማህበሩን ከበጎ አድራጎት ስራው ጋር በማዋሃድ ለ18 ዓመታት በራሱ አቅም ሰፊ ሰብአዊነት የተሞላበት ስራ ሲሰራ ቆይቷል።

1. የሴቶች እኩልነት

«የሴት ስራ በመስራቴ የተቀየረው መሀይምነቴ እንጅ ወንድነቴ አይደለም» የሚለውን የዙምራ አባባልን ተመርኩዞ በተግባር ስራ በችሎታ እንጅ በጾታ መሆን እንደሌለበት ለመላው አለም ማስተማር ተችሏል። ሴቶች ራሳቸውን ችለው በቤታቸውም ሆነ ከቤታቸው ውጭ ጉዳዮችን መወሰንና ማድረግ እንደሚችሉ በተግባር ማሳየት ተችሏል።

2. የህጻናት መብት

ህጻናት የመማር መብታቸው ተጠብቆ እግረተከል ከሆኑ ጀምሮ የቀለም ትምህርትንና ስነ-ምግባርን እየተማሩ ብቁ ትውልድ እንዲገኝ በራሱ አቅም የማሳደጊያ ተቋም በማቋቋም በነጻ በማስተማር ለትልቅ ደረጃ ማድረስ ተችሏል።

3. በጤናም ሆነ በእርጅና ምክንያት መስራት የማይችሉ ወገኖችን መርዳት

የአረጋውያን መንከባበቢያ ማዕከል በማቋቋም በየቀኑ ንጽህና፣ በቀን ሶስት ግዜ መመገብ እና ሙሉ የህክምና አገልግሎት በማድረግ ለረጅም አመታት ከማንም ሳይጠብቅ በራስ አቅም ሰብአዊ ስራ ሲሰራ ቆይቷል። «ሰው ሰውን አገዘ» የሚለው መርህ ተግባራዊ ሆኗል።

4. ሌላው በማህበረሰቡ ውስጥም ሆነ በውጭ ድንገተኛ ችግር

በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ችግር ላይ ለወደቁ ሰዎች፣ ለተፈናቃዮች እና ለመሳሰሉት በአቅሙ ልክ በሰፊው እገዛ ሲያደርግ የቆየ ተቋም ነው።

5. ጠብን ከነአካቴው ከምድረ-ገጽ መጥፋት

በውይይት የመፍታት ልምድን ያዳበረ እና ለሌሎችም ተምሳሌት በመሆን ከተለያዩ ተቋማት እውቅና ያገኘ። «ጠብንም እምናመጣው እኛነን ፍቅርንም እምናመጣው እኛ ነን»።

6. የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት

የሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤትን ሰርቶ ለመንግስት በማስረከብ ለ10 የገጠር ቀበሌዎች ልጆች የትምህርት እድል ማስፈን ተችሏል። «ሳይኖረው መስጠትን ያስተማረ ማህበረሰብ»።

7. የተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ

«መሬት ይዘቷን ጠብቃ እንድትቆይ እንጠብቃት» በሚል እሳቤ የአፈር ጥበቃ፣ የችግኝ ተከላ እና መንገድ ስራዎች ላይ ማህበረሰቡን በማንቀሳቀስ ውጤት እንዲመጣ ማድረግ ችሏል።

8. የተለያዩ ስልጠናዎች

በሰላም እና ልማት ጉዳይ ላይ በዙሪያው ላሉ የማህበረሰብ ክፍሎች የራሱን ተሞክሮ በማጋራት መልካም ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል።

9. ባህልና ቱሪዝም

ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ባህልን፣ መረዳዳትን፣ በጎ አስተሳሰብን እና ከገንዘብ ይልቅ ሰው እንደሚቀድም በማስተማር ተደራሽ ማድረግ ተችሏል። ይህንን ሀሳብ በወስደው በሌሎች ቦታዎችም ተመሳሳይ ማህበረሰብ መፍጠር ተችሏል።

ታሪኩን ይቀጥሉ

በሂደት ላይ ያሉ ፕሮግራሞችን ይመልከቱ፣ ታሪኮችን ያንብቡ ወይም ቀጣይ ስራውን ይደግፉ።