የአረጋዉያን እንክብካቤ ማዕከል
ንቁየአረጋዉያን እንክብካቤ ማዕከል በማዘጋጀት 12 አረጋዉያን ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ እና የጤና ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ በ አመት 2,000,000 ብር በጀት በጅቶ እየሰራ ይገኛል።
ስራችን
ሕይወቶችን የሚለውጡ እና የተሻለ ማህበረሰብ የሚገነቡ ንቁ ፕሮግራሞቻችንን ይመልከቱ።
የአረጋዉያን እንክብካቤ ማዕከል በማዘጋጀት 12 አረጋዉያን ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ እና የጤና ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ በ አመት 2,000,000 ብር በጀት በጅቶ እየሰራ ይገኛል።
በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ችግር ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ በማድረግ ችግራቸውን እንዲፈቱ ወይም እንዲያቃልሉ እንደ ችግሩ መጠን አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።
አዉራ አምባ ላይ ስልጠና ወይም ልምድ እሚያካፉሉ ሰዎችን በመመደብ ሴቶች የማድረግ እና የመወሰን መብት እንዳላቸው እና ህጻናት የመማር መብታቸው ተከብሮ እንዲያድጉ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ፕሮግራሞቻችንን የሚመሩ ዋና ዋና ግቦች
የሀገር ባለውለታ አረጋውያንን መርዳት፤ መንከባከብ እና ቀሪ ህይወታቸውን ተደስተው እንዲኖሩ ማስቻል።
ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ህጻናት የትምህርት እድል እንዲያገኙ ጥረት መደገፍ።
በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች ሙያና ንግድ ስልጠና እና የመጀመሪያ ድጋፍ።
የአውራ አምባ ማህበረሰብን ተሞክሮ ለሌሎች መማማሪያ ማድረግ።
የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራዎች ላይ መሳትፍ።
በሴቶች፣ ህጻናት እና አካል ጉዳተኞች ላይ የማህበረሰብ ግንዛቤ ስራ።
በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እርዳታ ማድረግ።
ታመው መታከሚያ ላጡ ወገኖች የህክምና ድጋፍ ማድረግ።
የተሻለ ማህበረሰብ መገንባት ተልዕኮአችንን ይቀላቀሉ። በፕሮግራሞቻችን ለመሳተፍ፣ በጎ ፈቃደኝነት ለመሰራት ወይም ስራችንን ለመደገፍ ብዙ መንገዶች አሉ።