ክንውኖቻችን

ዝግጅቶች እና ክንውኖች

50 አመት የለውጥ ስራ እና የማህበረሰብ ተጽዕኖ

  • ለ 30 አመታት 50 አረጋዉያንን ሙሉ በሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን እና በመንከባከብ ቀሪ ሂወታቸውን ተደስተው እንዲሄዱ ማድረግ ተችሏል።
  • አሁን ላይ 12 አረጋዊያንን ሙሉ ወጫቸውን በመሸፈን እና በመንከባከብ እየተወጣ ይገኛል።
  • በሴቶች እኩልነት፣ የህጻናት መብት እና መረዳዳት ላይ ተሞክሮውን ለሌሎች በማካፈል እና ስልጠና በመስጠት።
  • 120 ህጻናትን ተምረው ለቁም ነገር እንዲደርሱ በማድረግ ሂወታቸውን እንዲቀይሩ አድርጓል።
  • ለተፈናቃዮች ወደ 600,000 ብር ገደማ የአይነት ድጋፍ።
  • 32 ለመታከም አቅም ለሌላቸው የመታከሚያ ድጋፍ።
  • ለጎርፍ፣ እሳት እና ተመሳሳይ አደጋዎች ንብረት ላጡ ድጋፍ።
  • በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ ችግኝ ተከላ እና አፈር ጥበቃ ላይ ሰፊ ውጤት።
  • አዲስ ራዕይ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ለ10 ቀበሌዎች።
  • የሃገር በቀል የግጭት አፈታት ልምድ ለ3ተኛ ትውልድ እና ለሌሎች ማስተማር።

ከቀን መቁጠሪያ

ከአስተዳደር የታተሙ ዝግጅቶች

50ኛው ዓመት የምስረታ በዓል

October 18, 2022 · milestone

50ኛው ዓመት የምስረታ በዓል

የአውራ አምባ ማህበረሰብ የተመሰረተበትን 50ኛ አመት ሚያዚያ 29 ቀን 2014 ዓ.ም አክብሯል

የፌዴራል ምዝገባ

September 6, 2024 · achievement

የፌዴራል ምዝገባ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ጳጉሜ 01 ቀን 2016 ዓ.ም ተመዝግቧል

የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የተመሠረተው

January 1, 1972 · milestone

የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የተመሠረተው

የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የተመሠረተው በክቡር ዶክተር ዙምራ ኑሩ በፈለቁት የሐሳብ መነሻዎች ላይ በመመርኮዝ፣ የአርሶ አደር አባላት በአንድነት በመሰባሰብ ነው።

የአዲስ ራዕይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ

August 15, 2010 · achievement

የአዲስ ራዕይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ

የአዲስ ራዕይ ሁለተኛና መሰናዶ ደረጃ ትምህርት ቤትን በተሳካ ሁኔታ ገንብቶ ለመንግሥት ያስረከበ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ለሚገኙ 10 ገጠር ቀበሌዎች አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

የኅብረት ሥራ ማኅበር ምስረታ

January 1, 1986 · milestone

የኅብረት ሥራ ማኅበር ምስረታ

በጋራ ጥረትና በጋራ ሀብት ጠንካራ ከደካማ ተጋግዞ የሚኖርበት የኅብረት ሥራ ማኅበር ተመሰረተ።

የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል መቋቋም’

June 20, 1996 · achievement

የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል መቋቋም’

በጤናም ሆነ በእርጅና ምክንያት ለስራ ብቁ ያልሆኑ ወገኖችን በመንከባከብ ቀሪ ሂወታቸውን ተደስተው እንዲሄዱ ማድረግ እንዲሰችል የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል ተገንብቷል

የሽመና ኢንተርፕራይዝ

January 1, 1994 · milestone

የሽመና ኢንተርፕራይዝ

አባላት እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ብር በማዋጣት፣ ድጋፍ የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችል ገቢ በሽመና ሥራ ማመንጨት የጀመሩበት ወቅት።

ከ250,000 በላይ ሰዎች ሥልጠና አግኝተዋል

December 1, 2023 · milestone

ከ250,000 በላይ ሰዎች ሥልጠና አግኝተዋል

ስለ ሴቶች እኩልነት፣ ስለ ሕፃናት መብት እና ስለ ግጭት አፈታት ዙሪያ ከ250,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ሥልጠና የመስጠት እና የልምድ ልውውጥ የማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ተሳክቷል።

የክልል ሕጋዊ ዕውቅና

October 18, 2006 · recognition

የክልል ሕጋዊ ዕውቅና

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ጥቅምት 8 ቀን 1999 ዓ.ም ሕጋዊ ሰውነት ያለው ዕውቅና አግኝቷል

የፌዴራል ምዝገባ

September 6, 2024 · recognition

የፌዴራል ምዝገባ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ጳጉሜ 01 ቀን 2016 ዓ.ም ተመዝግቧል

1972

የማኅበረሰቡ መስረታ

የአውራ አምባ ማኅበረሰብ የተመሠረተው በክቡር ዶ/ር ዙምራ ኑሩ ሀሳብ አመንጭነት፣ አርሶ አደር አባላትን በማሰባሰብና በጋራ በመንቀሳቀስ ነው።

1978

የኅብረት ሥራ ማኅበር ምስረታ

በጋራ ጥረትና በጋራ ሀብት ጠንካራ ከደካማ ተጋግዞ የሚኖርበት የኅብረት ሥራ ማኅበር ተመሰረተ።

1986

የሽመና ኢንተርፕራይዝ (የሥራ ዘርፍ)

የማህበሩ አባላት እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ብር በማዋጣት፣ ድጋፍ የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ለመደገፍ የሚያስችል ገቢ በሽመና ሥራ ማመንጨት የጀመሩበት ወቅት።

1999

ሕጋዊ ዕውቅና

ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትሕ ቢሮ ጥቅምት 8 ቀን 1999 ዓ.ም ሕጋዊ ሰውነት ያለው ዕውቅና አገኘ።

2016

የፌዴራል ምዝገባ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ጳጉሜ 01 ቀን 2016 ዓ.ም ተመዘገበ።

ዋና ዋና ስኬቶች

በአገልግሎት ጉዟችን ውስጥ የተመዘገቡ ታላላቅ ታሪካዊ ምዕራፎች

የ30 አመት የአረጋውያን እንክብካቤ

ለ30 አመታት 50 አረጋውያንን ወጪያቸውን ሙሉ በሙሉ በመሸፈን እና በመንከባከብ ቀሪ ህይወታቸውን በደስታ እንዲያሳልፉ ማድረግ ተችሏል።

50+ ከ50 በላይ አረጋውያን እንክብካቤ ተደርጎላቸዋል

አስቸኳይ ድጋፍ

በተለያዩ አደጋዎች ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ወገኖች ወደ 600,000 ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ተደርጓል።

600K+ ብር የአይነት ድጋፍ ተደርጓል

የህጻናት ድጋፍ

ወላጆቻቸውን በሞት ያጡ ወይም ወላጆቻቸው የማስተማር አቅም ያልነበራቸው 120 ህጻናትን በመደገፍ ትምህርት እንዲያገኙ እና ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ተደርጓል።

120 ህጻናት ድጋፍ አግኝተዋል

የህክምና ድጋፍ

ለህክምና የሚያስወጣውን ወጪ መሸፈን ላልቻሉ 32 ሰዎች የህክምና ድጋፍ በማድረግ ከበሽታቸው እንዲያገግሙ ተደርጓል።

32 ሰዎች የህክምና ድጋፍ አግኝተዋል

የትምህርት መሰረተ ልማት

አዲስ ራዕይ ሁለተኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት ቤትን በመገንባት በአካባቢው ላሉ 10 ወረዳዎች ህጻናት የትምህርት እድል ማስፈን ተችሏል።

10 ወረዳዎች ተጠቃሚ ሆነዋል

የግጭት አፈታት

ማህበረሰቡ ላለፉት ከ50 አመታት በላይ ያካበተውን የግጭት አፈታት ልምድ ለሶስተኛው ትውልድ በስልጠና ማስተላለፍ ተችሏል።

50+ አመታት ልምድ

ዕውቅና እና ሽልማቶች

ለሠራናቸው ሥራዎች የተበረከቱልን የክብርና የምስጋና መግለጫዎች

የምስክር ወረቀቶች እና ሜዳሊያዎች

አውራ አምባ ማህበረሰብ እስካሁን ላከናወነው ተጨባጭ ስራ ከተለያዩ ተቋማት፣ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ብዙ የምስክር ወረቀቶች፣ ሜዳሊያዎች እና የምስጋና ደብዳቤዎች ተቀብሏል።

ማህበረሰቡ ከ1964 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የባህል መስህብ እውቅና ካገኘ በኋላ የስራ ባህልን፣ መረዳዳትን እና በጎ አስተሳሰብን በማስተማር የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ማድረግ ችሏል።

Our Impact by Numbers

Quantifying our contribution to society

300+
Children educated to self-reliance
50+
Elders cared for with dignity
250K+
People trained in equality & rights
600K+
Birr in emergency aid delivered
50
Years of community service
100%
Community-centered approach

ቀጥልን

ይህን የማህበረሰብ ታሪክ በመቀጠል ይደግፉን።